Pets

"ባለቤቱ ያላከበረውን..."

0 likes0 commentsAddis Ababa
ETB 0.00
Listed Price✓ 1 in stock

Description

ፀሀይዋ ገና ወደ ማዘቅዘቋ ነው። ሰፈሩ ዝም ብሏል፤ እኔ ግን ጣሪያ ላይ ሆኜ ከዲሹ ገመድና ከሲግናሉ ጋር እታገላለሁ። የኳስ ጨዋታ ስላለ ቤተሰቦቼ "ቶሎ አስተካክለው" ብለው ወጥጥረውኛል። ልክ ስራዬን ጀምሬ ጥቂት እንደቆየሁ፣ ሁለት ጎረቤቶቼ ብቅ አሉ። "ምነው? አልመጣ አለህ እንዴ?" እያሉ ወደ እኔ መጡ። እኔም የገጠመኝን ችግር በቅንነት ነገርኳቸው። ገና ንግግሬን ሳልጨርስ አንደኛው እጄ ላይ ያለውን መፍቻ ተቀበለኝ፤ ሌላኛው ደግሞ "ይሄ እኮ እንዲህ አይደለም..." ብሎ ገፋ አደረገኝ። የገዛ ቤቴ ጣሪያ ላይ ባይተዋር ሆንኩ። እኔን ወደ ዳር አስወጥተው፣ የእኔን መሣሪያ ይዘው፣ በእኔ ዲሽ ላይ መከራከር ጀመሩ። አንደኛው "ወደ ግራ አዙረው" ይላል፣ ሌላኛው "አይ ወደ ቀኝ ነው" እያለ ይጮኻል። እኔ መሃል ላይ ቆሜ የራሴን ስራ እንደ ፊልም አያለሁ። ጥቂት ቆይተው ግን የሆነው ነገር አስቂኝም አሳዛኝም ነበር። በክርክር መሃል ዲሹን ክፉኛ ስላወዛወዙት፣ የነበረውም ሲግናል ጨርሶ ጠፋ። በስተመጨረሻ "አይ ይሄ ዲሽ ራሱ ተበላሽቷል" ብለውኝ ጥለውኝ ወረዱ። ብቻዬን ስቀር ወደ ዲሹ ተመለስኩ። በረጋ መንፈስ፣ በራሴ እውቀትና ትዕግስት ለጥቂት ደቂቃዎች ሞከርኩት። ብዙም ሳይቆይ ምስሉ ጥራት ባለው ሁኔታ መጣ። **ትምህርቱ፦** በሕይወትህ ውስጥ በገዛ ጉዳይህ ላይ ሌሎችን አስቀድመህ ራስህን ወደ ዳር ካወጣህ፣ መጨረሻው ውጥንቅጥ መሆኑ አይቀርም። ምክር መቀበል መልካም ቢሆንም፣ የህይወትህን "መፍቻ" ግን ለማንም አትስጥ። መሪነቱን ለሌላው ከለቀቅክ፣ እነርሱ ተጣልተው አንተን ሜዳ ላይ ጥለውህ ይሄዳሉ። **የራስህን ህይወት ራስህ አስተካክል፤ ያኔ ሲግናሉ ጥርግርግ ብሎ ይመጣልሃል።**

A

Any phone market

Addis AbabaPosted 8 months ago · 14 views · All listings from this seller

Safety tips

  • Meet the seller in a safe public place and inspect before paying.
  • Avoid paying in advance, even for delivery.
  • Pay by bank transfer so there is a record, and only once you are satisfied.

Specifications

ConditionNew
CategoryPets
Stock1 available
LocationAddis Ababa
Posted8 months ago (18/01/2026)

Comments (0)

Log in to post a comment

No comments yet. Be the first to ask about this item!